ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል መርሆዎች

ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል መርሆዎች
1. ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል ሀገረ እስራኤል ስትመሰረት ካሰመረችባቸው ራዕይዎች ዋና ዋናዎቹ በአለም ከስደት የተመለሱት ህዝበ እስራኤሎች የመሰረቷት ሀገር ሁሉን በዲሞክራሲ የምታሳትፍ ሆና ለህዝቦቿ ሙሉ እኩልነት ታጎናጽፋለች

2. ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል የሰው ልጆችን ክብር መጠበቅ እንዳለበት በነፃነት አዋጅ የተቀመጡትን እሴቶች በማስፈጸም የሀገሪቱንና የህዝቦቿን ደህንት በቀጣይ በማረጋገጥ በትኩረት ትሰራለች

3. ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል የእስራኤል ዲሞክራሲ አገዛዝ እንዲጠነክር፣ የነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ በህዝቦች ዘንድ ፍትህና እኩልነት እንዲኖር በማድረግ ተግታ ትሰራለች፡፡
ሀቄሬን በግብ ካስቀመጠቻቸው አላማዎች ጥቂቶቹ፡-

በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በዘር፣ በፆታና ዝንባሌ ልዩነት ሳይደረግ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ነው

“የሰው ልጅና የዜጋ መብቶችን በህግ በማስጠበቅ ልዩ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ የፍልስጤም ዜጎችንና ከህዝብ የተገለሉትን በማካተት በተናጠልም ሆነ በቡድን መብታቸውን ማስጠበቅና ለሚደርስባቸው ልዩነቶችና የተሳሳቱ አመለካከቶች ማስተካከል

“የተለያዩ ብሔሮችን ባህልና ልምድ ማስተዋወቅና ማጠናከር እንዲሁም ተቻችሎ መኖርን ማጎልበት ናቸው፡፡

“የአናሳ ብሔሮችን መብቶች ማስጠበቅና በተለያዩ የዲሞክራሲ እንቅስቃሴዎችን በማሳተፍ የመብት ተጠቃሚዎች ማድረግ

“የእስራኤል ዜጎችን የመደራጀት አቅም በማጎልበት ነጻ ማህበረሰብ መፍጠር

“በፍትሐዊነት እና በተሳስቦ የሚኖር ህብረተሰብን በመገንባት በሀገር ውስጥና ከጎረቤት ሀገሮች ጋር በሰላም መኖር

“ከ“ሀቄሬን ሀሐዳሽ” ለእስራኤል የገንዘብ እገዛ ለማግኘት ቅድመ ሁኔታዎች

የእስራኤል ህግ በሚጠይቀው መሠረት ብቁ ሆኖ መገኘት
የ“ቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል ፖሊሲና ደንቦችን ያከበረ
በድጎማው ዙሪያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው “ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ዋና ስትራተጂዎች
ሀ. ማህበራዊ ለውጥ ተኮር ማድረግ
ለ. የእስራኤል ዲሞክራሲ እሴቶችን ተቋማት ማጠናከር
ሐ. ሀቄሬን በትኩረት የምትሰራባቸውን አራት መካከላዊ አላማዎች በቀጣይ ማስፈጸም ሲሆን እነዚህ የሰው ልጅ መብትና የዜጎች መብት ማስከበር፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ ማምጣት፣ የብሔሮችን ባህልና ሀይማኖት ማክበር፣ ተቻችሎ መኖርና አካባቢን ከቆሻሻና ከብክለት መከላከል ናቸው፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህጋዊ አካል
ሀ. ለህዝብ ጥቅም የተቋቋሙ በሚል በህግ የተመዘገቡ
ለ. ለህዝብ ይፋ በሆኑ ደንቦች ሲመሩ
ሐ. ገቢና ወጪ በተገቢው ሪፖርት የሚያደርጉ
መ. ገቢና ወጪ በደረሰኝ የሚይዙና የሀገር ገቢ ባለስልጣን ቢሮ በሚያዘው መሠረት ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ
ሠ. ከላይ የተጠቀሰው መመሪያ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ በጎ ድራጎት ድርጅቶችን አያካትትም

ከዚህ በታች በተዘረዘሩ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ ድርጅቶች “ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል እርዳታ አያገኙም

ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር ወግነው የሚንቀሳቀሱ
ዲሞክራሲን የሚፃረር ተግባር የሚፈጽሙ
የ67ቱን የፍልስጤሞች ግዛቶች የማይለቅ የመንግስት አቋም የሚደግፉና ህገወጥ ሰፈራዎች የሚደግፉ
የሰው ልጅ መብቶችን የሚጥሱ፣ አንድን ቡድን ከሌላው አብልጦ በማየት በመድሎና በልዩነት የሚሰሩ፣ አንድን ግለሰብ ከሌላው ዝቅ አድርገው የሚመለከቱ
በማህበረሰብም ሆነ በቡድኖች መካከል መተራመስ እንዲፈጠር የሚደግፉና የሚገፋፉ

ዘረኝነትን /የበላይነትን የሚገልጽ አነጋገር በመጠቀም ዜጋን ማዋረድ፣ ዝቅ ማድረግ፣ አንዱን ቡድን ፆታውን፣ ሃይማኖቱን፣ ዘሩን፣ አገሩንና ዝንባሌውን በመጥቀስ ማንቋሸሽ
የእስራኤል ህዝብ አገር አይገባውም ብሎ መተቸት፣ የፍልስጤም ህዝብ መብት አይገባውም ብሎ መተቸት፣ በእስራኤል የሚኖሩ አናሳ ብሔሮችን እኩልነት አያገኙም ብሎ ማሰብ
ከላይ የተጠቀሱት ተግባሮች ሁሉ “ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል የተወገዙ ናቸውና በእነዚህ የተሳተፈ ድርጅቶች እገዛ አያገኙም ማለት ነው፡፡

በBDS ማዕቀቦች የቄሬን አቋም ምንድን ነው?

ሀቄሬን ሀሳብ በነጻ በመግለጽ መፍትሔ የማምጣትን ሁኔታ ትደግፋለች ሀሳባቸውን፣ አቋማቸውን ለመልካም ዓላማ በሰላም የሚገልፁትን አካላት የሚወነጅሉትን በከረረ ሁኔታ ትቃወማለች፡፡
ትርምስና ጥፋትን መሠረት ያላደረጉ ስትራጂያዊ አሰራሮች በመጥፎ በመተርጎም ዓለም አቀፋዊ ማዕቀብ በእስራኤል ላይ የሚፈጽሙትን መንግስታትም ሆነ ድርጅቶች ሀቄሬን በጽኑ ትቃወማለች፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፋዊ ማዕቀቦች የእስራኤልን መንግስት በማዳከም የእስራኤልን ህዝቦች ሉአላዊነት ለማሳጣት የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው፡፡ ሀቄሬን ሀሐዳሻ በእስራኤል ላይ አለም አቀፍ ማዕቀቦች በመጣል ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ደጋፊ አትሆንም የዚህ አይነት ተግባር የሚፈጽሙ ድርጅቶችንም አታግዝም በሌላ በኩል “ሀቄሬን ሀሐዳሻ” ለእስራኤል የፍልስጤም ግዛቶች ለቆ የማይወጣ መንግስትን ታወግዛለች፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ህገወጥ ሰፈራዎችን የሚቃወሙና በእነዚህ ህገወጥ ሰፈራዎች በተመረቱ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ሀቀሬን እገዛ ታደርጋለች፡፡”